በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ አምስት ሺህ ቤተ-እሥራኤላውያን ወደ አገረ እሥራኤል ሊያቀኑ ነው

*** ቤተ እሥራኤላውያኑን ወደ እሥራኤል ለማጓጓዝ ከስምምነት ላይ የተደረሰው፤ ውልደታቸው ኢትዮጵያ የሆነው የኢሚግሬሽን ሚኒስትር 'ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎች ወደ እሥራኤል ካልመጡ ከመንግሥት አባልነቴ እለቃለሁ' የሚል ማስጠንቀቂያ በመስጠታቸው መሆኑ ተነግሯል።

Community

Newly arrived Jewish Ethiopians disembark a plane upon landing in Israel on a special flight from Ethiopia on December 3, 2020 in Tel Aviv, Israel. Source: Getty

በሰሜን ኢትዮጵያ በፌዴራል መንግሥት ወታደሮችና በሕወሓት ታጣቂዎች መካከል እየተካሔደ ያለውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ 5,000 ቤት እሥራኤላውያን ወደ እሥራኤል እንዲዘልቁ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። 

ለስምምነቱ መደረስ ብርቱ አስተዋፅዖ ያደረጉት የኢትዮጵያ ተወላጇ የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ኒና ታማኖ ሻታ እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አየለት ሻኬድ መካከል ከአዋኪ ድርድር በኋላ ማክሰኞ ዕለት በተደረሰ መግባባት ሳቢያ ነው።

Community
Immigration Minister Pnina Tamano-Shata. Source: Getty

በስምምነቱ መሠረት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የሥጋ ዘመድ እሥራኤል ውስጥ ላላቸው ይሆናል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እሥራኤላውያን ቁጥር ከ7,000 እስከ 12,000 እንደሚደርስ ይገመታል። አብዛኛዎቹ የሚገኙት ትግራይ ውስጥ ሲሆን የተቀሩት ጎንደርና አዲስ አበባ ይገኛሉ። 

ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እሥራኤሎችን አስመልክቶ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል "ሕይወታቸው ለአደጋ ተጋልጧል የሚለው የተጋነነ ነው፣ በቀርቡ ወደ እሥራኤል ከመጡት ውጥ ብዙዎቹ የቤተ እሥራኤል ዝርያ ያላቸው አይደሉም" የሚል አስተያየት መሰንዘራቸው ተዘግቧል። 

ከ1997 ወዲህ ባሉት ጊዜያት ውስጥ 30 ሺህ ያህል ቤተ እሥራኤላውያን ወደ እሥራኤል መግባታቸውን የእሥራኤል ተቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሪፖርት ያመለክታል።   


1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now