በአሮጌው የኢትዮጵያ ብር ኖት መገበያየት ከዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 22 - 2013 ጀምሮ የሚያከትም መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
ብሔራዊ ባንኩ የአሮጌው የኢትዮጵያ ብር ኖት ቅያሬም ታህሳስ 6 - 2013 እንደሚያበቃ ገልጧል።
በዛሬው ዕለት የሚያበቃው የአሮጌ ብር ኖት ግብይት ለብር ኖት ቅያሪው መፋጠን የበኩሉን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክትና ለብር ቅያሬው የቀሩት ቀናት 15 ቀናት ብቻ መሆናቸውን ባንኩ አስገንዝቧል።
በቀሪዎቹ ሁለት ሳምንታት አሮጌዎቹ የብር ኖቶች በእጃቸው የሚገኙ ሰዎች ከታህሳስ 6 በፊት ወደ ባንክ ሄደው ሕጋዊ ቅያሪ እንዲያደርጉ ብሔራዊ ባንኩ በድጋሚ ጥሪ አድርጓል።
አሮጌ የብር ኖቶችን በአዲስ የብር ኖቶች መቀየር የተጀመረው ከመስከረም 6 - 2013 ጀምሮ ነው።

