የአረብ ሊግ በህዳሴ ግድብ ላይ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ሚዛናዊነት የጎደለው እና ኢፍትሐዊ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
መንግሥት የአረብ ሊግ ውሳኔ የዓባይን ወንዝ በትብብር እና በዘላቂነት ለመጠቀም የሚያስችል አለመሆኑንና ዓለም አቀፍ ሕጎችን የሚጻረር ነው ሲል ተችቶታል።
ውሳኔው የአረብ ሊግ አባል ሀገራት የዓባይ ወንዝን አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የነበረ አቋም ካለማወቅ የመጣ መሆኑን ገልጿል ፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሌሊቱን ባወጣው መግለጫ።
የሕዳሴው ግድብ ኢትዮጵያውያንን ከድህነት የሚያወጣ፣ የኃይል አቅርቦት እና የምግብ ዋስትና የሚረጋገጥበት ፕሮጀክት ነው ፡ ይህንን ማንም ሊገነበዘበው ይገባል ብሏል።
አባይ የጋራ ሀብት እንጂ የተናጠል የግብጽ እና የሱዳን ሀብት አለመሆኑን፤ ይሁን እንጂ የተፋሰሱ ሀገራት በትብብርና በውይይት የውኃ ደህንነት ማረጋገጫ መንገድ እንደሆነ የኢትዮጵያ ጽኑ እምነት ነው ያለው መግለጫው ኢትዮጵያ የሁለቱን ሀገራት ስጋት ከግምት ውስጥ ያስገባ፣ የታችኞቹን የተፋሰስ ሀገራትን በጋራና በትብብር መንፈስ እንጠቀም መርህን አሁንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቋል፡፡
በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚደረገውን ድርድር የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በሚገባ ሳያጤኑ ያሳለፉትን ሚዛናዊነት የጎደለው ውሳኔ በድጋሜ እንዲመለከቱትም ጠይቋል፡፡ የውኃ ሙሌቱም በተያዘለት መርኃግብር ይከናወናል ብሏል።
[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]

