Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE starting June 12 2026

የአውሮፓ ኅብረትና ኤምባሲዎች ስለ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የጋራ መግለጫ አወጡ

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ 25 የኅብረቱ አባል አገራት ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች (ኦስትሪያ፣ ቤልጅየም፣ ቡልጋሪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ አይርላንድ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ስሎቬንያ፣ ስፔን እና ስዊድን) እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት አባል ያልሆኑ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ በመሆን ስለ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

gettyimages-2239583752-612x612.jpg
European Union Flag. Credit: Douglas Sacha/Getty Images

የሀገራቱ ተወካዮች በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውን ምርጫ በይፋ በመቀበል፣ የምርጫ ሂደቱ እንዲሳካ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለምርጫ ሠራተኞች፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለዕጩዎች እና ለሲቪል ማኅበራት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ያላቸውን ሚና በማድነቅ ስለ ምርጫው የሚያቀርቡትን ሪፖርቶች በትኩረት እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል።

መግለጫው ምርጫው ከተካሄደ በሁለተኛው ቀን የወጣ ሲሆን፣ በቀኑ ምርጫ ያልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች ሁሉ በቀጣይ የመሳተፍ ዕድል እንዲያገኙ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ዲፕሎማቶቹ በጋራ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ዜጎች በምርጫው የመሳተፍ መብታቸው መከበር እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎች የምርጫ ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።


1 min read

Published

By Demeke Kebede

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now