SKIP TO MAIN CONTENT

ፌስቡክ አውስትራሊያ ላይ ጥሎ የነበረውን የዜና ስርጭቶች ዕገዳ ነገ ሊያነሳ ነው

*** ፌስቡክ የተወሰኑ ለውጦችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

ነገ ዓርብ ፌብሪዋሪ 26 ፌስቡክ የአውስትራሊያ የዜና ገጾች ላይ ጥሎ የነበረውን ዕገዳ እንደሚያነሳ በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ አስታወቁ።

አክለውም "ከነገ ጀምሮ የተወሰኑ ለውጦችንም ታያላችሁ፤ ፌስቡክ እንዲያ ብሎ ነግሮናል" ሲሉ ለሬዲዮ 2GB ዛሬ ማምሻው ላይ ተናገረዋል።

ፌስቡክ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ አታሚዎችና ተጠቃሚዎች የአገር ውስጥና የባሕር ማዶን ዜናዎችና ታሪኮች ማጋራትና መመልከት እንዳይችሉ ዕገዳ ጥሎ አለ።

ለዕገዳው መጣል አስባብ የሆነው የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት ከጥቂት ቀናት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በዛሬው ዕለት ይሁንታ ያገኘው የሚዲያ ረቂቅ ድንጋጌ ነበር።

ረቂቅ ድንጋጌው ፌስቡክ ገጾቹ ላይ ለሚያሰፍራቸው የአውስትራሊያ ዜናዎች ክፍያ እንዲፈጽም ግድ የሚል ነው።

ሆኖም ዕገዳ ከጣለ በኋላ በፌዴራል መንግሥቱና ፌስቡክ መካከል በተደረጉ ድርድሮች ረቂቅ ድንጋጌው ላይ ማሻሻያዎች በመደረጋቸው ከአግባቢ ስምምነት ላይ መድረስ ችለዋል።     

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now