አንገስ ቴይለርን በ17 ድምፅ ብልጫ ለአዲሱ የሊብራል ፓርቲና የተቃዋሚ ቡድን መሪነት ያበቃው የምርጫ ድምፅ ውጤት በውጥረት የተመላ እንደነበርም ተመልክቷል።
አቶ ቴይለር ከ51 የሊብራል ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ውስጥ 37 ድምፅ በማግኘት በማያወላዳ ድምፅ አሸናፊ ለመሆን የበቁት የወ/ሮ ሊ ደጋፊዎች ወደ ቴይለር ካምፕ በመቀላቀላቸው በመሆኑ እንደሁ ለSBS News ተጠቁሟል።
ድል የተነሱት ሱዛን ሊ "የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤዬን ለአፈ ጉባኤው አቀርባለሁ። ቀጥሎ የሚሆነው ምን እንደሚሆን አላውቅም። ከቤተሰቤ ጋር ጊዜዬን ለማሳለፍ፤ ከሕዝባዊ የአደባባይ ሕይወት ጠቅልዬ እገለላሁ" ሲሉ የፖለቲካ ዓለም ስንብት ቃላቸውን እንሆኝ ብለው በታመቀ የሐዘን ቃል ቀጣዩን የሕይወት ጊዜያቸውን አመላክተዋል።

ለሊብራል ፓርቲ ምክትል መሪነት ከተወዳደሩት ጄን ሂም፣ ቴድ ኦብራያን እና ዳን ቲሃን ውስጥ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባሏ ጄን ሂሁም በድል ነሺነት የአዲሱ ሊብራል ፓርቲ መሪ ምክትልት ለመሆን በቅተዋል።

