ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የመጀመሪያዎቹ 26 ተመላሽ አውስትራሊያውያን ከአፍጋኒስታን ወጥተው የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ጦር ሠፈር እንዲያርፉ መደረጉን አስታወቁ።
ከተመላሾቹ ውስጥ የአውስትራሊያና አፍጋን ዜጎችና ዓለም አቀፍ ኤጀንሲዎችን የወከሉ የውጭ አገር ሠራተኞች ይገኙበታል።
አቶ ሞሪሰን በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ በረራ የተመላሾች ቁጥር እንዲጨምር ለማድረግ መንግሥት ጥረቶችን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ይሁንና በረራዎቹ የሚወሰኑት እንደ አየር ንብረቱና ካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሚከሰቱት ተግዳሮች እንደሚወሰኑም አመላክተዋል።
የፌዴራል መንግሥቱ 3,000 ሰብዓዊ ቪዛዎችን ለአፍጋኒስታንውያን መመደቡም ተነግራል።
Share

