አውስትራሊያ በሴቶች 4x100m ነፃ የኦሎምፒክ ዋና ውድድር የዓለም ሬርኮርድን ባስመዘገበ ሰዓት በማሸነፍ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያን አግኝታለች።
የአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ ያዥ ኬት ካምቤል፣ እህቷ ብሮንቴ፣ ኢማ ማክኪኖንና ሜግ ሃሪስ ዛሬ እሑድ ባካሔዱት ውድድር 29 ደቂቃ ከ69 ሰከንድ በቶኪዮ የመዋኛ ማዕከል በማሸነፍ አጠናቅቀዋል።

ቀደም ሲል በ2018 የጋራ ብልፅና ውድድር ወቅት አስመዝግባው የነበረው የዓለም ሪርከርድ 3:30.05 ነበር።
በውድድሩ ካናዳ በሁለተኛነት፤ ዩናይትድ ስቴትስ በሶስተኛነት ፈጽመዋል።
ቴኒስ ኦሎምፒክ
አውስትራሊያዊቷ አሽ ባቲ በሴቶች የነጠላ መጀመሪያ ዙር ውድድር በስፔይኗ ሳራ ሶሪቤስ ቶርሞ ተረትታ ከኦሎምፒክ ውድድር ተሰናብታለች።
አሽ ባቲ የተረታችው 6-4, 6-3 በሆነ ውጤት ነው።


