ዶናልድ ትራምፕ ጃኑዋሪ 20 በሚካሔደው የጆ ባይደን ፕሬዚደንታዊ ቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ላይ አልገኝም አሉ

*** ተመራጭ-ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የትራምፕን በቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ላይ አልገኝም ማለትን "ጥሩ ነገር ነው፤ ለአገሪቱ ማፈሪያ ናቸው" ብለውታል።

Trump

Donald Trump salutes after he was sworn in as president in Washington, DC, 20 January 2017. Source: EPA

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጃኑዋሪ 20 በሚካሔደው የጆ ባይደን ፕሬዚደንታዊ ቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደማይገኙ አስታወቁ።

17ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት አንድሩ ጆንሰን በ1869 በተኪያቸው 18ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዩልየሲስ ግራንት ፕሬዚደንታዊ ቃለ መሃላ ላይ አልገኝም ካሉ 152 ዓመታት በኋላ ፕሬዚደንት ትራምፕ ሁለተኛው ፕሬዚደንት ሆነዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ይህንኑ በዓርቡ የቲዊተር መልዕክታቸው ገልጠዋል።

Trump
Source: Donald J. Trump

ተመራጭ-ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የትራምፕን በቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ላይ አልገኝም ማለትን "ጥሩ ነገር" ነው ብለውታል።

አቶ ባይደን "ወደ እዚህ እየመጣሁ ሳለ በቃለ መሃላ ሥነ ሥር ዓቱ ላይ የማይገኙ መሆኑን ወደ እዚህ እየመጣሁ ነው። እኔና እሳቸው ከምንስማማባቸው ጥቂት ነገሮች አንዱ ይህ ነው። የእሳቸው አለመገኘት ጥሩ ነገር ነው። ለአገሪቱ ማፈሪያ ናቸው" ሲሉ ከነበሩበት ዊልሚንግተን - ዴላዌር ተናግረዋል።

Joe Biden
Joe Biden listens during an event at The Queen theatre in Wilmington, Delaware on 8 January. Source: AP

ባይደን የምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በሥነ ሥርዓቱ ላይ መገኘትን በመልካም ጎኑ እንደሚቀበሉት ገልጠዋል።

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now