"ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃን የምታለማው ለቅንጦት ሳይሆን የሕይወት ጉዳይ በመሆኑና እንደ አገርና ሕዝብ የመኖር ጥያቄ በማስገደዱ ነው" - ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው

*** የአምባሳደሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥራ ኃላፊዎች ዓመታዊ ስብሰባተጠናቀቀ

Foreign Affairs

Gedu Andargache, Minister of Foreign Affairs of Ethiopia Source: PD

ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለይቶ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መንቀሳቀስ እንደሚገባው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አሳሰቡ።

ላለፉት 15 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአምባሳደሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥራ ኃላፊዎች ዓመታዊ ስብሰባ ትናንት ተጠናቀቀ።

ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የተጠናቀቀው 2012 ዓመት በዓለም ላይ በአወንታዊና አሉታዊ ጎኑ የዲፕሎማሲ ሥራ የተፈተነበት ነበር። ሚኒስትሩ በኢንቨስትመንት፣ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ በቱሪዝም፣ በፖለቲካና ሌሎች ዘርፎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ዲፕሎማቱ ተግቶ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

“በመላው ዓለም በሚደረግ የዲኘሎማሲ እንቅስቃሴ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ፍላጎትና ግብ  ነጸብራቅ መሆን ይገባቸዋል” ብለዋል።

ዲፕሎማቱ በስራው የኢትዮጵያን ሰላም፣ ብልጽግ፣ ዴሞክራሲንና ህብረብሔራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት መደገፍ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በቀጣይ ዓመት ዲፕሎማቶች በተመደቡበት አገር ነባራዊ ሁኔታውን ከግምት በማስገባት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን በማስቀደም መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ ዲፕሎማቶች በተወከሉባቸው አገሮች ያሉትን ነባራዊ ሁኔታዎች አስቀድመው ከአገራዊ ጥቅም አንጻር በመገምገም መስራት ይኖርባቸዋል። “ከውጭ ግንኙነት የትኩረት አቅጣጫ አኳያ በባህልና በተፈጥሮ ሃብት ከተሳሰሩት አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉም አመልክተዋል። “የቀጠናው ተለዋዋጭነቱ እየጨመረ በመምጣቱ በዚህ በኩል ከፍተኛ ሥራ መስራት ይጠይቃል” ብለዋል ሚኒስትሩ።
Foreign Affairs
Ethiopian diplomats Source: PD
በሚሲዮኖች ላይ እየታየ ያለው አሳፋሪ ተግባር ሊቆምና ሊታረም የሚገባው መሆኑንም አስገንዝበዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃን የምታለማው ለቅንጦት ሳይሆን የሕይወት ጉዳይ በመሆኑና እንደ አገርና ህዝብ የመኖር ጥያቄ በማስገደዱ ነው።

ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ የያዘችውን የፍትሃዊነት አቋም አምባሳደሮች ለዓለም ማስረዳታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።      

ኢትዮጵያ ያዘጋጀችውን የ10 ዓመት ዕቅድ ጠንቅቆ በማወቅ መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም ነው አቶ ገዱ የገለጹት።

“ኮቪድ-19 በቱሪዝም ዘርፍ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ ቢኖርም አገራት የአየር ክልሎቻቸውን እየከፈቱ በመሆኑ በንቃት መከታተል ያስፈልጋል” ብለዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው የሰው ኃይል ስምሪትን ማዘመን፣ ማብቃት፣ ስነ-ምግባር፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደም፣ ወዳጅ አገሮችን ማፍራት ትኩረት የሚያሻቸው መሆኑም ተመልክቷል።


Share

Published

By Stringer Report

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service