የቀድሞው መሪ በጥይት የተመቱት ዛሬ ዓርብ ጁላይ 8 / ሐምሌ 1 እሑድ ለሚካሔደው ለሊብራል ዲሞክራት ፓርቲ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ የቅስቀሳ ንግግር እያደረጉ ሳለ ነው።
ሁኔታውን አስመልክተው የጃፓን ባለስልጣናት እንደገለጡት አቤ በአየር ትራንስፖርት ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ትንፋሽ እንዳልነበራቸውና የልብ ትርታቸው ቆሞ እንደነበር ጠቅሰዋል።
የህዝብ ብዙኅን መገኛው NHK የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በጥይት ተመትተው እንደወደቁ የሚያሳያውን ምስል ለእይታ አቅርቧል።
የአቤ በጥይት መመታት ለሕዝብ ይፋ የሆነው ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው።

Former Prime Minister Shinzo Abe bleeds from chest after being shot in front of Yamatosaidaiji Station on July 8, 2022 in Nara, Japan. Source: Getty
የአደጋውን ዜና የሰሙትና በምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ የነበሩት የቀቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ የምርጫ ቅስቀሳቸውን አቋርጠው በሂሊኮፕተር ወደ ቶኪዮ አቅንተዋል፤ ሁሉም የካቢኔ አባላት የምርጫ ቅስቀሳቸውን አቋርጠው ቶኪዮ እንዲገቡ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
አቤ በ2020 በጤና ምክኛት ከተቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።
አቤ በተለይም ጃፓንን ከጦርነት የሚያርቀውን ሕገ መንግሥት ለመለወጥና የአገሪቱን የመከላከያ ኃይል ኮሪያና ቻይናን በብርቱ በሚቀናቀን መልኩ ለመቅረፅ እንዲያስችል በፓርላማ ማሳለፋቸው በሕዝብ ዘንድ ፅኑዕ ቁጣን፣ በተወሰኑት ዘንድም የከፋ አተያይን አስነስቶባቸው ነበር።
የአቤ ደጋፊዎች በበኩላቸው የጃፓንና ዩናይትድ ስቴት ስን ኝኙነት ጠንካራ ደረጃ እንዲደርስ ማድረጋቸው አንዱ የመታሰቢያ አሻራቸውን እንደሆን ተናግረዋል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ፣ የዩናይትድ ስቴት ስ ባለስልጣናትና የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በክስተቱ መደናገጣቸውንና ከልብ ማዘናቸውን ገልጠዋል።