ፈረንሳይ ከዩናይትድ ስቴትስና አውስትራሊያ አምባሳደሮቿን ጠራች

*** "የልገሳ ማጓጓዙ እንዲፋጠን የፍተሻ ጣቢያዎች ቁጥር ተቀንሷል" ቢልለኔ ስዩም

French president Emmanuel Macron.

French president Emmanuel Macron. Source: Getty

ፈረንሳይ ከአውስትራሊያና ዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደሮቿን ወደ ፓሪስ ጠርታለች።

ለፈረንሳይ ብርቱ የሆነ የዲፕሎማሲ ተቃውሞ እርምጃ የወሰደችው አውስትራሊያ፣ ዩናይትድ ስቴትስና እንግሊዝ የጋራ መከላከያ ስምምነት በማድረጋቸው ሳቢያ አውስትራሊያ 12 የባሕር ሰርጓጅ መርከቦችን ለመገንባት ከፈረንሳይ ጋር ያደረገችውን የ$90 ቢሊየን ዶላርስ ስምምነት በማፍረሷ ነው።

የአውስትራሊያ መንግሥት በአዲሱ የሶስትዮሽ መከላከያ ስምምነት በዩናይትድ ስቴትስና እንግሊዝ እገዛ በኑክሊየር ኃይል የሚንቀሳቀስ ስምንት ባሕር ሰርጓጅ መርከቦችን ለመገንባት ይበቃል። 

የሶስትዮሹን ስምምነት ተከትሎ አውስትራሊያ የ$90 ቢሊየን ዶላርስ ስምምነቷን ማፍረሷና ሶስቱ አገራት ከአዲስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ፈረንሳይ ያወቀችው  ስምምነቱ ለሕዝብ ይፋ ከመሆኑ ከሁለት ሰዓታት ቀደም ብሎ መሆኑ የፈረንሳዩን ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮንን በእጅጉ አስቆጥቷል። 

በአውስትራሊያ የፈረንሳይ አምባሳደር ዤን ፒየር ቲቦት ፈረንሳይ "ከጀርባዋ ተወግታለች፤ ይህ እጅግ አመኔታ ያጎደለ ክሕደት ነው" ሲሉ ለአገር ውስጥ ሚዲያ በምሬት ገልጠዋል።   

በከፍተኛ አመራር ደረጃ አውስትራሊያ ባለ ኑክሊየር ኃይል ሰርጓጅ መርከብ ትሻ እንደሆነ በፈረንሳይ በኩል መጠየቁንና ፈረንሳይ ምንም ምላሽ እንዳለገኘች ጠቅሰዋል።

አያይዘውም፤ ከቶውንም የአውስትራሊያ መከላከያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራት ከአንድ ወር በፊት ከፈረንሳይ አቻዎቻቸው ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ከፍ ስለማድረግ ተነጋግረው እንደንበረ አመልክተዋል። 

የሁለቱ አገራት ወታደራዊ ትብብር ላይ ክለሳ የማድረጉን ዕሳቤ ወደ ጎን እንደማይሉት ጠቁመው "ምናልባትም ንዴታችን ምን ያህል የጋለ እንደሆነ አትረዱን ይሆናል" ሲሉም ተናግረዋል።

ፈረንሳይ ከአሜሪካ አምባሳደሯን ስታስወጣ የአሁኑ በታሪክ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። እርምጃውን አስመልክቶ የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጡት መግለጫ "በሪፐብሊኩ ፕሬዚደንት ጥያቄ መሠረት የዩናይትድ ስቴትስና አውስትራሊያ አምባሳደሮቻችን በአስቸኳይ ወደ ፓሪስ ለምክክር እንዲመለሱ ወስኛለሁ" ብለዋል።    

***

ቢልለኔ ስዩም የጠሚር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ፤ ሐሙስ በተከናወነው በሳምንታዊው የጠሚር ጽሕፈት ቤት የውጭና አገር ውስጥ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ቢልለኔ ስዩም እንዳሉት በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች ሰብአዊ እርዳታዎች እንዲደርሱ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በአማራና አፋር ክልሎች በሕወኃት ወረራ የተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግቦች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርሱ በባሕርዳር፣ ደሴ፣ ጎንደርና ሰመራ ከተሞች ማስተባበሪያዎች መቋቋማቸውን ገልፀዋል።

ቢልለኔ እንዳሉት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ለሚያደርሱ ረጂ ድርጅቶች እንቅስቃሴ መቀላጠፍ ሲባል ሰባት የነበሩት የፍተሻ ጣቢያዎች ወደ ሁለት ዝቅ መደረጋቸውንም አረጋግጠዋል።

"በሰሜን ወሎ አካባቢዎች አሸባሪው ሕወኃት ሰላማዊ ሰዎችን እንደ ዋሻ እየተጠቀመ ነው።" ያሉት ቢልለኔ ይህ የከፋ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን አክለዋል።

ወደ ትግራይ ሰብአዊ እርዳታዎችን ይዘው የተጓዙ የዓለም አቀፍ ተቋማት 466 ተሽከርካሪዎች ውስጥ ከአርባ ያነሱት መመለሳቸውንም ጠቅሰዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራምም በጉዳዩ ላይ በትዊተር ገፁ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይፋ አድርጓል።

በቅርቡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ታጣቂዎች እጃቸውን እንዲሰጡ የቀረበውን ጥሪ መንግስት እንዴት ያየዋል በሚል ለተነሳ የጋዜጠኞች ጥያቄ " በአሸባሪው ሕወኃት አሁንም ድረስ ወጣቶች ተገደው ወደ ጦርነት ይገባሉ።  የትግራይ እናቶችና ነዋሪዎች እንደሌላው የአገሪቱ ክፍል የሰላም አየር ሊተነፍሱ ይገባል። ስለዚህ ለጥቂት የሕወኃት ተፈላጊ ወንጀለኞች ሲባል ብዙዎቹ ወጣቶች የጦርነት ሰለባ መሆን የለባቸውም" ሲሉ የመንግስታቸው አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


3 min read

Published

By NACA


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now