የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ቀጣይነት ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቀጠሮ ተያዘለት

የኢትዮጵያ ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር

GERD talks

Source: Courtesy of PD

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌትና ውኃ አለቃቀቅ ደንብ  ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከነሀሴ 15 - 22 የሶስትዮሽ ስብሰባ አካሂደዋል።

ከሱዳን በኩል የትሳትፎ ማረጋገጫ ከተሰጠ ሶስቱ አገራት ቀጣይነ ድርድራቸውን መስከረም 4 - 2013 ሊያካሂዱ እንደሚችሉ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቋል፡፡

የሶስቱ አገራት የውኃ ሚኒስትሮች ለአንድ ሳምንት ታድመው የተወያዩ እንደሆነና በየአገራቱ ተወካይ ባለሙያዎች በኩል የሕዳሴ ግድብ ሙሌትና ውኃ አለቃቀቅ ደንብን የተመለከተ ሙያዊ የድርድር ሪፖርት መቅርቡን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጧል።

ይኼው ስብሰባ በተካሔደበት ወቅትም የደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች በታዛቢነት የተገኙ ሲሆን ከአፍሪካ ሕብረት የተወከሉ ባለሙያዎችም መሳተፋቸውን ተነግሯል።፡

ቀጣዩን የድርድር ሂደት አስመልክቶም ለደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር፤ እንዲሁም ለአፍሪካ ሕብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀ መንበር ዶ/ር ናዴሊ ፓንዶል ለመላክ መስማማታቸውን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር መግለጫ አመልክቷል፡፡

 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now