የፌዴራል መንግሥቱ የ$1 ቢሊየን የሥራ ስልጠና ዕቅዱን ይፋ አደረገ

ሥራ አጥነት ለመቀነስም ለሰልጣኞችና የሥራ ላይ ለማጆች ደመወዝ መደጎሚያ የሚውል $1.5 ቢሊየን በታካይነት ተመድቧል።

Government unveils $1 billion JobTrainer plan to skill post-coronavirus Australia in high-demand areas

Source: AAP

የፌዴራል መንግሥቱ ለስልጠና የመደበው በጀት የምጣኔ ሃብት ድቀት ተከስቶ ባለበት ወቅት ወደ ሥራ ዓለም ለሚሰማሩ 350,000 ያህል ወጣት አውስትራሊያውያን አዲስ ክህሎት እንዲያዳብሩ ነጻ ስልጠናዎች መስጫነት ይውላል።     

ሐሙስ ይፋ በሆነው የአዲስ ክሎት ማዳበሪያ ፕላን ከትምሀርት ቤት ወደ ሥራው ዓለም የሚዘልቁ ወጣቶች የጤና ክብካቤ፣ ትራንስፖርት፣ የፋብሪካና ችርቻሮ ዘርፍ ስልጠናዎችን መውሰድ ይችላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የክህሎት ስልጠና ኮርሶቹን ለማካሄድ የጋራ ብልፅግናው $500 ሚሊየን ዶላርስ ላይ የክፍለ አገር መንግሥታት ተጨማሪ $500 ሚሊየን ዶላርስ እንዲያክሉ ጠይቀዋል። ምንም እንኳ አንዳቸውም የክፍለ አገር መንግሥታት በየፊናቸው የድርሻቸውን ወጪ እንደሚሸፍኑ እስካሁን ድረስ በይፋ ባይገልጡም፤ ዓርብ ዕለት በተካሄደው የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ላይ ከስምምነት ደረሰዋል።

ስልጠናዎቹ በቴፍ ኮሌጅና የግል ማሰልጠኛ ማዕከላት በኩል የሚሰጡ ይሆናሉ። የስልጠና ደረጃቸውም ከምስክር ወረቀት  III እና IV እስከ ዲፕሎማ ኮርሶች ይደረሳል።     

የትኞቹ ዓይነት የስልጠና ዘርፎች ይበልጡኑ የአውስትራሊያ ምጣኔ ሃብት ፈጥኖ እንዲያንሰራራ እንደሚያግዝ የመለየቱ ኃላፊነትም ለብሔራዊ ክህሎቶች ኮሚሽን ተሰጥቷል።

በሌላም በኩል የፌዴራል መንግሥቱ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ እየተፈጠረ ያለውን ሥራ አጥነት ለመቀነስ ለሰልጣኞችና የሥራ ላይ ለማጆች ደመወዝ መደጎሚያ የሚውል $1.5 ቢሊየን በታካይነት መመደቡን በምጣኔ ሃብት ሪፖርቱ አስታወቋል።

ድጎማው ቀደም ሲል በወርኃ ማርች ላይ ከ 200 በታች ሠራተኞች ላሏቸው መለስተኛ ንግዶች እንደሚቸር የተገለጠ ቢሆንም በአሁኑ መግለጫ እስከ ማርች 2021 ተራዝሟል። 

በወርኃ ማርች ላይ አቶ ሞሪሰን ድጎማው ለ120,000 የሥራ ላይ ተለማማጆችና ሰልጣኞች ሥራ አጋዥ እንደሚሆን የገለጡ ቢሆንም፤ መንግሥታዊው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ ግና 47,000 የንግድ ተቋማት ቀጥረው ያሉት የሥራ ላይ ተለማማጆችና ሰልጣኞች 81,000 ያህል ብቻ ነው።

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now