የግሬት ሲድኒ ነዋሪዎች ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው በአንዳንድ የቤት ውስጥ ስፍራዎች የፊት ጭንብልን የግድ ማድረግ አለባቸው

የግሬት ሲድኒ ነዋሪዎች ( ዎሎንጎግ ፤ ሴንትራል ኮስት እና ብሉ ማውንቴንስ ) ጨምሮ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው በአንዳንድ የቤት ውስጥ ስፍራዎች የፊት ጭንብልን የግድ ማድረግ አለባቸው ፡፡ በሽቀጣ ሸቀጥ መሸጫዎች ፤ በገበያ ማእከሎች ፤ ፊልም ቤቶች ፤ ቲያትር ቤቶች ፤ በህዝብ መጓጓዣ፤ በውበት ሳሎኖች እና የጸጉር ቤቶች ፤ በእምነት ስፍራዎች እንዲሁም የጌም መጫወቻ ቦታ ሁሉ ነዋሪዎች የፊት ጭንብልን ( ማስክ ) የግድ ማድረግ አለባቸው ፡፡

Father helps daughter with mask -  Getty Images - Morsa

Source: Getty Images - Morsa

ከሰኞ ጃንዋሪ 4 ጀምሮ  የፊት ጭንብልን (ማስክ) ያላደረጉ ሰዎች የ $200 ቅጣት ይጠብቃቸዋል ፡፡ እድሜያቸው ከ12 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የማድረግ ግዴታ ባይኖርባቸውም ፤ የኒው ሳውዝ ዌልስ ባለስልጣናት ግን ሁሉም ሰው እንዲያደርግ ያበረታታሉ ፡፡

የምግብ ባለሙያዎች እና የካዚኖ ሰራተኞች የፊት ጭንብል (ማስክ) ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡

በአምልኮ ስፍራዎች ፤ በሰርግ እና በቀብር ስነስርአት ላይ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ከ100 እንዳይበልጥ የተወሰነ ሲሆን በአራት ስኩዬር ሜትሮች ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ በተግባር ውሏል ፡፡ የምሽት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ዝግ እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡ጂሞች የሚያስተናግዷቸው ስዎች ቁጥር ከ 50 ወደ 30 ዝቅ ብሏል ፡፡

በውጭ የሚደረጉ ክዋኔዎች እና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ቁጥር ከ500 እንዳይበልጥ የተወሰነ ሲሆን ፤ የመግቢያ ቲኬቶችን ቆርጠው ፤ ተቀምጠው የሚሳተፉባቸው የቤት ውጭ እንቅስቃሴዎች የታዳሚዎች ቁጥር ከ 2000 እንዳይበልጥ ተወስኗል ፡፡

የሚኖሩበትን ክልል እና ግዛት አዳዲስ መረጃዎች በተመለከተ፦

ኒውሳውዝ ዌልስ ፦ https://www.nsw.gov.au/covid-19 

ኩዊንስላንድ ፦ https://www.covid19.qld.gov.au/

ዌስተርን አውስትራሊያ ፦ https://healthywa.wa.gov.au/Articles/A_E/Coronavirus

ሳውዝ አውስትራሊያ ፦ https://www.covid-19.sa.gov.au/

ኖርዘርን ቴሪቶሪ ፦ https://coronavirus.nt.gov.au/

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ፦https://www.covid19.act.gov.au/

በአውስትራሊያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ በመካከላቸው የ 1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ ይኖርባቸዋል ፡፡ በተጨማሪም በጋራ የመሰባሰብ ገደብን በተመለከተ የየክልላቸውን ህግ መመልከት ይኖርባቸዋል ፡፡የብርድ ወይም የጉንፋን ምልክቶችን ካሳዩ ከቤትዎ አይውጡ ፤ ይልቁንም የኮሮናቫይረስ ምርመራን እንዲያደርግልዎ ሀኪምዎ ጋር ይደውሉ ፤ወይም coronavirus Health Information Hotline on 1800 020 080 ወይም በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

ዜናዎችን እና መረጃዎችን በተመለከተ በ63 ቋንቁዎች ከ sbs.com.au/coronavirus.

 

 

 


Share

Published

Updated

By SBS Radio
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የግሬት ሲድኒ ነዋሪዎች ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው በአንዳንድ የቤት ውስጥ ስፍራዎች የፊት ጭንብልን የግድ ማድረግ አለባቸው | SBS Amharic