ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጉዳይ አገሪቱ ስለደረሰበት ደረጃ አብራርተዋል።
"ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈጥሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት‼️
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከተጀመረ ባጭር ጊዜ ውስጥ ባርካታ ለውጥ መጥቷል፤ እንደሳቸው ገለፃ "በግብርናው ዘርፍ፤ በጤና ዘርፍ በካንሰር በጣም አመርቂ ውጤት አግኝተንበታል" ብለዋል።
አክለውም "በአዲስ አበባ ከተማ ግድያዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው፣ በቴክኖሎጂ በመታገዝ እየሰራን ስላለው በቅርቡ በዝርዝር የምንገልጸው ይሆናል" ብለዋል።
ዓለም ላይ ያላቸውን ደመናን ወደዝናብ የቀየሩ አገራት ጥቂት አገራት ናቸው ያሉት ጠሚሩ "እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ አየዋለሁ ብዬ ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ ይሄ የተከማቸ ደመና በተመረጠ ሁኔታ ማዝናብ መቻልን ነው፤ አሁን ኢትዮጵያ ይሄንን አቅም ገንብታለች፤ ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈጥሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው። በግልጽ በሚቀጥሉት ሳምንታት እናስመርቀዋልን፤ ወይንም እናስጀምረዋለን። ኢትዮጵያ ደመናዋን ተጠቅማ ዝናብ ማዝነብ ችላለች" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ቋንቋዎቻችንን አብዛኛው ማሽኖች ከተለማመዱት፣ ብዙ ነገሮችን መስራት እንችላለን" ሲሉ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል።
[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]

