ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመፍታት አቅም እንዳላት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ገለጡ

***የአሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይን ጨምሮ በርካታ አገራት ዜጎቻቸው ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ እያሳሰቡ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ መገኘት ለበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

Homeland Report

Chinese State Councilor and Foreign Minister Wang Yi (L) and Ethiopian DPM anf Foreign Minister Demeke mekonnen. Source: MoFA spokesperson Office

ዛሬ ረፋዱን አዲስ አበባ አበባ የገቡት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

አቶ ደመቀና ዋንግ ዪ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ዋንግ “በኢትዮጵያ ጉብኝት አገራቸው በኢትዮጵያ ያላትን መተማመን እንዲሁም ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መንግስት ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ነው” ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ዋንግ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ቻይና የምትቃወም መሆኑንና ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ጉዳይ ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሳቸው መንገድ የመፍታት ብቃቱ አላቸው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ቻይና ከኢትየጵያ ህዝብና መንግስት ጋር በመርህ ላይ የተመሰረትና የጸና የወዳጅነት ግንኙነትን አድንቀው “ቻይና ለኢትዮጵያ ልዑላዊነት እና የግዛት አንድነትን አስመልክቶ ለምታራምደው ጽኑ አቋም ኢትዮጵያ ታደንቃለች” ብለዋል፡፡

አክለውም እንደማንኛው ጊዜ ሰላም እና የተረጋጋች በሆነቸው የአገራችን መዲና፣ አዲስ አበባ ክቡር ዋንግ ይን በመቀበል ለማስተናገድ በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ክቡር አቶ ደመቀ ገልጸዋለ።

የአሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይን ጨምሮ በርካታ አገራት ዜጎቻቸው ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ እያሳሰቡ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ መገኘት ለበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ቻይናና ሩሲያ በአዲስ አበባ የሰላም ስጋት የለም ካሉ አገራት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

(ደመቀ ከበደ - አዲስ አበባ)


2 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now