በጠቅላይ ሚኒስትር ኣቢይ አሕመድ የሚመራውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መዋቅርና አደረጃጀት መመሪያን ግብር ላይ ለማዋል ሶስት የፌዴራልና ክልል ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል።
1) የፌዴራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክትትል ኮሚቴ፤
2) የፌዴራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የፀጥታ ኮሚቴ፤
3) የክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ ናቸው።
ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል።
በዚህም መሠረት፤
የፌዴራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክትትል ኮሚቴ
1. አቶ ደመቀ መኮንን (ም/ጠ/ ሚኒስትር እና የው/ጉ/ሚኒስትር) - ሰብሳቢ
2. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - አባል
3. አቶ በለጠ ሞላ - አባል
4. አቶ አቶ ቀጀላ መርዳሳ - አባል
5. ኢንጂነር አይሻ መሐመድ - አባል
6. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ - አባል
7. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ - አባል
8. አቶ ሬድዋን ሁሴን - አባል
9. አቶ ምትኩ ካሳ - አባል
የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የፀጥታ ኮሚቴ
1. ጄ/ል ብርሃኑ ጁላ( የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም) - ሰብሳቢ
2. የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል - አባል
3. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር - አባል
4. የፍትህ ሚኒስትር - አባል
5. የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት - አባል
የክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ
1. የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር - ሰብሳቢ
2. የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር - ም/ሰብሳቢ
3. የክልሉ የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ - አባል
4. የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር - አባል
5. የክልሉ ፍትህ ቢሮ/ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ - አባል ይሆናሉ።

