የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዜጎች ላይ የተፈፀሙ ጭፍጨፋዎችን የሚያጣራ ልዩ ኮሚቴ እንዲቋቋም ወሰነ

*** “የአርባ ምንጭ ሙዝ”፣ “የአዊ ድንች” እና “የጨንቻ አፕል” ምርቶች አዳዲስ መለያና ስያሜ ተሰጣቸው

News

Members of the Parliament participate in a session in the city of Addis Ababa, Ethiopia. Source: Getty

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ በምክር ቤቱ የበላይ አመራር የሚሰየሙ እና ብዝኀነትን ታሳቢ ያደረገ ልዩ ኮሚቴ የዜጎችን ጭፍጨፋ እንዲመረምር ውሳኔ አስተላልፏል።

የዕለቱን መርኃ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ የጀመረው ምክር ቤቱ፤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አስተላልፏል፡፡

በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እጅግ የኮነነው ምክር ቤቱ፤ በአገራችን በየትኛውም ክልልና አካባቢ በሲቪል ዜጎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

በየደረጃው ያለው አመራር አካል፣ የጸጥታ አካል እና የፍትሕ ተቋም የህዝቡን ደህንነትና ሠላም በጥብቅ እንዲያስከብር፣ አጥፊዎች ለሕግ ተጠያቂነት እንዲቀርቡ እንዲደረግ ወስኗል።

ከመንደራቸውና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በአስቸኳይ እንዲሰራ የወሰነው ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ በወንድማማችነት፣ በአብሮነት እና በአንድነት እንዲቆሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

መለያና ስያሜ 

በግብርና ምርቶቹ ብራንድ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር) "ዛሬ ብራንድ የተደረጉ ምርቶች በግብርና ሚኒስቴር በአስር ዓመታት ውስጥ ትኩረት ተሰጥቷባቸው በትኩረት እየሰራባቸው ያሉ ስትራቴጂክ ምርቶች ናቸው" ብለዋል።

ምርቶቹ ብራንድ እንዲደረጉ ሃሳቡን ላመነጩት እና እንዲተገበር ላደረጉት የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ፍሬዓለም ሺባባዉም ምስጋና አቅርበዋል።
News
Source: P.Record
የግብርና ምርቶቹ ብራንዶች ይፋ በሆኑበት መርሃ ግብር በምርቶቹ እሴት ሠንሠለቶች ደካማ የግብይት ትስስር፣ የገበያ መሰረተ ልማት እጦት እና በእሴት ሰንሰለት ውስጥ ገበያውን የሚያዛቡ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዳሻቸው ዋጋ መተመናቸውን እንዲያቆሙ በኅብረት ስራ ፣ በንግዱ ዘርፎች ያሉ እና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ርብርብ እና ቅንጅት ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ተገልጧል፡፡

በብራንድ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል እና የአማራ ክልል የኅብረት ስራ ኤጀንሲ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
News
Officials. Source: P.Record
በቀጣይም በሶማሌ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች በቅደም ተከተል የሚገኙት የፍየል፣ ማንጎና ቀይ ሽንኩርት ምርቶች ብራንድ ለማድረግ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን እንቅስቃሴ መጀመሩ አስታውቋል።

ብራንድ የተደረጉት ምርቶች በኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን አነሳሽነት በአይነታቸው የተለዩ በኀብረት ሥራ ማኅበራት አባላት የሚመረቱ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡


Share

Published

By Stringer Report

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service