ኢትዮጵያ ቢትኮይንን መሰል የዲጂታል መገበያያ ገንዘቦችን መጠቀም ከለከለች

***የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳሳወቀው "ምናባዊ ንብረትን ወይም ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ" ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ተግባር እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡

News

Representation of Bitcoin cryptocurrency and an illustrative chart. Source: Getty

የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ ይደነግጋል።

በተጨማሪም በክፍያ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003 መሠረት በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም ብሏል ተቋሙ በመግለጫው፡፡ባንኩ ከጥናት ተረድቻለሁ እንዳለው በአሁኑ ወቅት ከህግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ፣ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል።

በተጨማሪም ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል ብሏል።እየተስተዋለ ያለው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን እንዲጠብቅ ያሳሰበው ተቋሙ ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል፡፡


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now