" ጋዜጠኛን ከሕግ ውጭ ሰውሮ ማቆየት ይቁም " ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጠየቀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቀናት በፊት ማንነታቸውን ባልገለጹ የመንግስት ሰዎች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ ተይዞ መወሰዱንና የት እንዳለ አለመታወቁን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ መልስ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።

News

Jouurnalist Gobeze Sisay. Source: ESAT

ማህበሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ ጋዜጠኛው በምን ጥፋት ተጠርጥሮ እንደተያዘና ምክንያቱ ምን እንደሆነ በግልጽ ካለመነገሩ በላይ የት እንደሚገኝ አለመታወቁ ከዚህ ቀደምም ማሕበሩ ሲቃወመው የቆየው በሌሎች ጋዜጠኞችም ላይ የደረሰው መሰል ድርጊት አካል ሆኖ እንዳገኘው አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የማህበሩ መስራች አባል መሆኑን በማሳት ታፍኖ ተወስዶ እንዲሰወር የተደረገው የዓለማችን የፕሬስ ነጻነት ሳምንት በሚከበርበት ወቅት መሆኑ መንግስት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ጥቃት እንደከፈተ ያስቆጥረዋል ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያጠፋው ጥፋት ቢኖር እንኳን የፍትህ አካላት እንደማንኛውም ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር ሊውልና ዳኝነት ሊሰጠው ሲገባ ከተያዘበት ቀን አንስቶ የት እንደሚገኝ ሳይገለፅ መቆየቱ የመብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን መንግስት ይህን ያልተገባ አደገኛ አዝማሚያ በጋዜጠኞች ላይ ማድረስ እንደመብት የቆጠረው አስመስሎታል ሲል ኮንኗል።

ማህበሩ ፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ለምን እንደታሰረ፣ የት እንደሚገኝ እና የተያዘበት ምክንያት በግልጽ እንዲነገር አፅንኦት ሰጥቷል።

[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]


1 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now