SKIP TO MAIN CONTENT

የአዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ካቢኔ አባላት ሹመቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅድቅ ተቸራቸው

*** የካቢኔ አባላት ሹመቱቶቹ በአብላጫ ድምፅ የፀደቁት 2 ተቃውሞና 12 ድምፀ ተአቅቦ ገጥሟቸው ነው

Homeland Report
Newly elected parliament members of Ethiopia participate during the swearing-in ceremony, in the city of Addis Ababa, Ethiopia, on October 04, 2021. Source: Getty

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ኦክቶበር 06 ያቀረቡት የካቢኔ አባላት ሹመቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታን አግኝቷል።

በአብላጫ ድምፅ ይሁንታ የተቸራቸው ሾመቶች በድምፅ አሰጥታ ወቅት 2 ተቃውሞና 12 ድምፀ ተአቅቦ አግኝቷቸዋል።

በዚህም መሠረት፦

  •  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ደመቀ መኮንን
  • መከላከያ ሚኒስትር - ዶ/ር አብረሃም በላይ
  • የገንዘብ ሚኒስትር - አህመድ ሽዴ
  • የሥራና ክህሎት ሚኒስትር - ሙፈሪሃት ካሚል
  • ግብርና ሚኒስትር - ኡመር ሁሴን
  • የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር - ኢ/ር አይሻ መሃመድ
  • የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር - ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ
  • የትምህርት ሚኒስትር - ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
  • የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር - ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
  • የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር- አቶ ገብረመስቀል ጫላ
  • የኢንዱስትሪ ሚኒስትር- አቶ መላኩ አለበል
  • የሰላም ሚኒስትር- አቶ ብናልፍ አንዷለም
  • የፍትህ ሚኒስትር- ዶ/ር ጌዴዎን ጤሞጢዎስ
  • የጤና ሚኒስትር- ዶ/ር ሊያ ታደሰ
  • የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር- አቶ በለጠ ሞላ
  • የቱሪዝም ሚኒስትር- አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ
  • የገቢዎች ሚኒስትር-  አቶ ላቀ አያሌው
  • የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር - ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
  • የማዕድን ሚኒስትር- ኢ/ር ታከለ ኡማ
  • የፕላንና ልማት ሚኒስትር - ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
  • የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
  • የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር - አቶ ቀጄላ መርዳሳ ሆነዋል።

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now