የ2013 ዓ.ም “ ዘጠነኛው የበጎ ሰው ሽልማት”እሑድ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አዳራሽ ተካሂዶ ነበር። በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናው፡፡
ለዘጠነኛ ጊዜ በተዘጋጀው የ 2013 ዓ.ም የበጎ ሰው የሽልማት ፕሮግራም ላይ በ አስር ዘርፎች ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት፡
1. በኪነጥበብ ዘርፍ በዕውቀቱ ስዩም
2.በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ
3 . በቅርስና ባሕል ዘርፍ ቢላሉል ሐበሽ ሙዚየም
4.በመምህርነት ዘርፍ ዶ/ር ልዑልሰገድ አለማየሁ
5.በሚዲያና በጋዜጠኝነት ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ
6. በበጎ አድራጎት አቶ አማረ አስፋው
7. በሳይንስ ዘርፍ ኤመሬትስ ፕሮፌሰር አለማየሁ
8. በንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ አቶ በላይነህ ክንዴ
9. መንግስታዊ የስራ ኃላፊነት በብቃት በመወጣት ዘርፍ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
10.ለኢትዮጵያ መልካም ስራ ከሰሩ የዳያስፖራ ማኅበርሰብ አባላት ዘርፍ አቶ ኤልያስ ወንድሙ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡
በዚህ ዓመቱ የ2013 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች በተጨማሪ በየዘርፉ እጩ ሆነው ለቀረቡት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የ2013 ዓ.ም የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ (ነፍስኄር) ጸሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ ሆነዋል፡፡

