"የተወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ ሃሳብ ለመለወጥ መንግሥት እየተገደደ ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

*** የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

Demeke Mekonnen , Deputy Prime Minster of Ethiopia and Minster of Foreign Affairs.

Demeke Mekonnen , Deputy Prime Minster of Ethiopia and Minster of Foreign Affairs. Source: Getty

የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው "አሸባሪው ሕወሓት" እየፈጸመ ባለው ጥቃት የተነሳ የታለመለትን ዒላማ ሊያሳካ እንዳልቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የተወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ ሃሳብ ለመለወጥ እያስገደደው እንደሆነም መንግስት አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

"ሕወሓት በከፈተው ጥቃት ከአፋርና አማራ ክልሎች ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉና በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን እንዲያጡ አድርጓል ፣ እየፈጸመ ያለውን ሰብዓዊ ግፍም የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎታል" ብሏል መግለጫው።

በመሆኑም ተጨማሪ ጥፋትና ግፍ እንዲፈጸምና ዜጎች ኑሯቸው እንዲመሰቃቀል መንግስት የማይፈቅድ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል የተወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ ሃሳብ ለመለወጥ እያስገደደው ነው ብሏል።

 [ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


1 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now