በኢሰመኮና ተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቢሮ ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጥምር የሰብዓዊ ምርመራ ሪፖርት 16 አገራት እንደሚቀበሉት ተናገዋል፡፡
አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣ ሉግዘንበርግ፣ኔዘርላንድ፣ ኒውዝላንድ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን እና እንግሊዝ በጣምራ ሪፖርቱ ላይ የጋራ መግለጫ ያወጡ ሀገራት ናቸው።
በመግለጫቸው ሁለቱ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቋማት [ኢሰመኮ እና የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቢሮ] በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ዙሪያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ያወጡት ሪፖርት ገለልተኛ እና ተጠያቂነትን ሊያሰፍን የሚችል መሆኑን እንደገለፁ አል ዓይን ዘግቧል።

