"የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ በጥልቅ አሳስቦኛል" ዩኔስኮ

*** የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ጥበቃ ተቋም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናትን በቅርስነት የመዘገባቸው እ.አ.አ በ1978 ነው

Ethiopians Second Jerusalem  Lalibela.

Ethiopians Second Jerusalem Lalibela. Source: Getty

የተባበሩት መንግስት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ጥበቃ ተቋም የሆነው ዩኔስኮ የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን ተከትሎ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት ውቅር አብያተ ክርስትያናቱ ለጉዳት እንዳይጋለጡ አሳስቦኛል ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎችን እየወረረ እንደሆነ የተገለፀው ሕወሓት ላሊበላ ከተማ ታጣቂዎቹ መግባታቸው ተሰምቷል።

ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት በቅርሱ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ማስጠንቀቁ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ዩኔስኮ መግለጫ አውጥቷል።

ዩኔስኮ በመግለጫው በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት እጅግ ድንቅ የሆኑት የዓለም ቅርሶች ከጉዳት ሊጠበቁ የሚገባው በመሆኑ አብያተ ክርስትያናቱ ከየትኛውም ጥቃት እንዲሁም በውስጡ የሚገኙ ባህላዊና ኃይማኖታዊ ቁሳቁሶች ከዝርፊያ ሊጠበቁ ይገባል ብሏል።

ላሊበላ የሰው ልጅ ድንቅ ጥበብ፣ ትጋትና ሰላም መገለጫ ስፍራ ነው ያለው ዩኔስኮ በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከአለት የተፈለፈሉ አስራ አንድ ውቅር ቤተ ክርስትያናት የሚገኙበት ስፍራ ነው ብሏል።

ዩኔስኮ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናትን በፈረንጆቹ 1978 ነው በቅርስነት የመዘገባቸው።

በቅርሶቹ አጠባበቅና ደህንነት ጉዳት ከሕወሓት የተሰማ አሁናዊ መረጃ ባይኖርም የኢትዮጵያ መንግስት "ለትግራይ ሕዝብ ለክረምት እርሻ ዝግጅትና ሰብአዊ ድጋፍ ምቹነት ተብሎ የታወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ሕወሓት የጎረቤት ክልል ሕዝቦችን ሕይወት እየቀጠፈበትና እያፈናቀለበት" ነው ሲል ጠቅሶ ውሳኔውን ለመሻር እንደሚገደድ ትናንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኩል ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


1 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now