የዓለም ምግብ ድርጅት ከ13 ሚሊየን በላይ ለምግብ ዋስትና እጦት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን እርዳታውን ለማዳረስ የ426 ሚሊየን ዶላር አስቸኳይ ድጎማ እንደሚሻ አስታወቀ

*** ዋና መሥሪያ ቤቱ ኖርዌይ የሆነው የወርቅ ፍለጋና ልማት ኩባንያ አኮቦ ማዕድናት ኢትዮጵያ ውስጥ መጠነ ሰፊ የወርቅ ምርት ፈቃድ ሊያገኝ ነው።

Aid convoy.

Aid convoy. Source: Getty

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ድርጅት ከ13.6 ሚሊየን በላይ ለምግብ ዋስትና እጦት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን የምግብ እርዳታ ለማዳረስ $426 ሚሊየን አስቸኳይ ድጎማ እንደሚሻ ትናንት ሴፕቴምበር 7 አስታወቀ። 

ችግሩ ጎልቶ የተከሰተባቸው ክፍለ አገራትም የአፋር፣ አማራና ትግራይ መሆናቸውንም ጠቅሷል። 

ለምግብ ዋስትናው እጥረት በዋነኛ አስባብነት ወታደራዊ ግጭት፣ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የበረሃ አንበጣ፣ የገበያ መስተጓጎል፣ የምግብ ዋጋ መናርና የኮረናቫይረስ ተጠቃሽ ሆነዋል። 

የዓለም ምግብ ድርጅት በአፋር ለ 530,000 በአማራ ለ250,000 ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ ካገኘም በእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ልክ አቅርቦቱን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ገልጧል። 

ትግራይ ውስጥ  አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚሹ 5.2 ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሶ፤ በዓለም ምግብ ፕሮግራም የሚመራ 3,500 ሜትሪክ ቶንስ ምግብ፣ የነዳጅ፣ የጤናና መጠለያ ቁሳቁሶችን የጫኑ ከ100 በላይ የጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ መዝለቃቸውን አስታውቋል። 

ይህንኑ አስመልክቶ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ዳይሬክተር ማይክል ዳንፎርድ "የዓለም ምግብ ድርጅት ቅልፈታችን ደህንነቱ ተጠብቆ ትግራይ መድረስ እንዲችል በፌዴራልና የአፋር ክፍለ አገር ባለ ስልጣናት የተደረገልንን ትብብር በመልካም ጎኑ ተቀብሎታል" ሲሉ አመስግነዋል።  

በማከልም "ተጨማሪ ገንዘብ አሁኑኑ ካላገኘን የምግብ ክፍፍላችንን መጠን ልንቀንስ ሲልም በከፋ መልኩ በመጪዎቹ ወራት ለአፋር፣ አማራና ትግራይ 4 ሚሊየን ሰዎች  አቅርቦታችንን ልንገታ እንገደዳለን" በማለት አስጠንቅቀዋል።

አኮቦ ማዕድናት

ዋና መሥሪያ ቤቱ ኖርዌይ የሆነው የወርቅ ፍለጋና ልማት ኩባንያ አኮቦ ማዕድናት ኢትዮጵያ ውስጥ መጠነ ሰፊ የወርቅ ምርት ፈቃድ ሊያገኝ ነው።

ኩባንያው ከ10 ዓመት የፍለጋ ሥራ፣ ከከፍተኛ ደረጃ የሰገሌ ቁፋሮና የቅርብ ውይይት በኋላ ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የፈቃድ ጥየቃ ማመልከቻ ያስገባ መሆኑን አስታውቋል።   

ሂደቱን ተከትሎም የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ከአኮቦ ጋር በትብብር መሥራቱን ጠቁመው "የማዕድን ፈቃዱ በሚቀጥለው ሳምት፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ከዕልባት ላይ ይደርሳል" ብለዋል።

የመጠነ ሰፊ ማዕድን ፈቃድ የሚሰጠው ለመጀመሪያ ጊዜ ለ20 ዓመት በቀጣይነትም ለ10 ዓመት ነው። 

 

 


2 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now