SKIP TO MAIN CONTENT

ማይጨውና መቅደላን ጨምሮ በደሴና ተንታ ግንባር ከተሞች ተለቀቁ

*** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለጊዜው ወደ ቢሮ ሥራቸው ስለመመለሳቸው፣ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንደተነጋገሩና ምስጋናም እንዳቀረቡ ገልጠዋል።

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

የደሴና ተንታ ግንባር ከተሞች ከሕወሓት እጅ ወጥትተው በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው ወታደራዊ መግለጫ አስታወቀ።

በመግለጫው መሠረት የተእቀቁት ከተሞች፤

  • በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች 
  • በተንታ ግንባር ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ናቸው።

በሌላም በኩል ከጦር ግንባር ወደ ቢሮ ሥራቸው ለጊዜው መመለሳቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና ጂቡቲ መሪዎች ጋር ሰፋ ያለ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውንና ምስጋናም ማቅረባቸውን ገልጠዋል። 

በሕወሓት በኩል በሁለት ቀናት ውስጥ የሕወሓት ጦር 158 ኪሎ ሜትሮችን በእግር መጓዙንና በ10 ሺህ የሚቆጠር የመንግሥት ጦር ለሕልፈት ሕይወት መዳረጉን በቃል አቀባዩ በኩል የገለጠ ሲሆን፤ ሰሞኑን በቁጥጥሩ ስር ያደረጋቸው ወይም ከእጁ ወጥተው በመንግሥት ሠራዊት እጅ ስለገቡ ከተሞች አላነሳም። 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now