የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ነሐሴ 4 2013 ባወጣው መግለጫ ቀደም ሲል ወስዶት የነበረውን የተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃ ማብቃቱን አስታወቀ።
መንግሥት በመግለጫው የአገር መከላከያ ሠራዊታችን፣ የክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች፤ የኃይል እርምጃ መውሰድ እንዲችሉ አቅጣጫ የተቀመጠላቸው መሆኑን ገልጧል። ለተለያዩ የማሕበረሰብ አባላትም ከሠራዊቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል።
አያይዞም "ውጊያው የትግራይን ሕዝብ ምሽግ ካደረገው እኩይ ኃይል ጋር እንጂ ከትግራይ ጋር አይደለም" ብሏል።
በሕወሓት በኩል ለጊዜው የተሰጠ የአጸፋ መግለጫ ባይኖርም ዘግይቶም ቢሆን የአቋም መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
Share

