የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን እንዳስታወቀው በምሥራቅና ውጫሌ ግንባሮች ቀደም ሲል በሕወሓት ቁጥጥር ስር የነበሩ ከተሞች በመንግሥት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
በዚህም መሠረት፤
- በምሥራቅ ግንባር የዞብል ሰንሰለታማ ተራሮችን ጨምሮ የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞች
- የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከተሞች
- በውጫሌ ግንባር የአምባሰል ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎች በመንግሥት ቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሌላ በኩል የሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በመንግሥት በኩል የህወሓት ጦር "የቆቦ ወልድያ መንገድ ስለተዘጋበት በጋሸናና ላሊበላ" በኩል ሰብሮ ለመውጣት ሙከራ ስለማድረጉ የተገለጠውን ሲያስተባብሉ "ጋሸናና ኣምባሰል ዛሬ ስለሆነውና ስለሚቀጥለው ሌላ ጊዜ እንመለሳለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
Share

