አንቶኒ ብሊንከን ከኖቬምበር 15 እስከ 20 ባሉት ቀናት ከሶስት የአፍሪካ አገራት ጋር ሊመክሩ ነው
ሚኒስትሩ ጉዟቸውን ወደ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ሴኔጋል እንደሚያደርጉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል።
የአሜሪካው ከፍተኛ ዲፕሎማት በናይሮቢ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ይመክራሉ።
ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ሱዳንን የተመለከቱ አካባቢያዊና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዲሁም ኮቪድ 19 የመሪዎቹ ግንኙነት ማጠንጠኛ ሃሳቦች መሆናቸውን የብሊንከን መስሪያ ቤት ገልጿል።
በቀጣይም ብሊንከን አቡጃ ደርሰው ከናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ ጋር ከዛም በሴኔጋል ዳካር ላይ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳልን አግኝተው ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ።
Share

