የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 33 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህም ካለፉት ሁለት ተከታታይ ወራት አንፃር የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት የሸቀጦች የወጪ ንግድ ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ16 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ 972 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ተችሏል፡፡ እንደሳቸው ማብራሪያ በ2014 በጀት ዓመት በመጀመሪዎቹ ሶስት ወራት በመንግሥት የገቢና ወጪ፣ በሸቀጦች የወጪ ንግድ እንዲሁም በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ጥሩ ውጤት መመዝገቡ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የጦርነት ሁኔታ ለመሸከምና ጫናዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ኢኮኖሚን ለመገንባት መልካም ጅማሮዎች መኖራቸውን ያመለክታል ብለዋል።
ሕወኃት በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ያደረሰው ወድመት እጅግ ከፍተኛ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ክልሎቹን መልሶ ለማቋቋም የሁሉንም አካል ከፍተኛ ርብርብ ጠይቀዋል፡፡
(ደመቀ ከበደ - አዲስ አበባ)

