የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

News

Ethiopia National Disaster Risk Management Commissioner Mitiku Kassa. Source: Getty

የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጠ።

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌደራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፥ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በእንጅባራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ ማብራራታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now