"2700 የጤና ተቋማት በደረሰባቸው ውድመት አገልግሎት መስጠት አቁመዋል" ጤና ሚኒስቴር

*** የጤና ሚኒስቴር ለሕብረተሰቡ ቀጣይነት ያለዉ አገልግሎት ለመስጠትና አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ እንዲያስችል ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Homeland Report

Dr Lia Tadesse, Ethiopian Minister of Health. Source: Getty

"ጤና ሚኒስቴር 2700 የጤና ተቋማት በደረሰባቸው ውድመት አገልግሎት ማቆማቸውን አስታወቀ፤ ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ለማቋቋምና መልሶ ስራ ለማስጀመር ሁሉን-አቀፍ የድጋፍ ጥሪም አቅርቧል

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ “አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ካደረሰው ሰብዓዊና ሞራላዊ ጥፋት በተጨማሪ ህዝብ የሚገለገልባቸውን የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቀቋማት፤ የህክምና ግብዓት ማከማቻ ተቋማትን እና ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት አውድሟል፡፡ የህክምና መሳርያዎችን እና ሌሎች ግብዓቶችንም ጭኖ በመውሰዱ ዝርፍያ እና ጉዳት ፈጽሟል፡” ብሏል፡፡

በጤና ተቋማት ላይ የደረሰው ወድመት በተለይ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የመሰረታዊ እና ድንገተኛ ህክምና አግልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ አስተጓጉሏል ያለው ሚኒስቴሩ እስካሁን ባለው መረጃ ከ2700 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡ ሲሆን በአሁን ወቅት በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ አከባቢዎች ሲካተቱ ዉድመት የደረሰባቸዉ ቁጥር ከዚህ እንደሚያሻቅብ ግምቱን ገልጧል፡፡

“በጤና ተቋማቱ ላይ በተከሰተዉ መጠነ ሰፊ ወድመት ምክንያት በርካታ ዜጎች የጤና አግልግሎት የሚያገኙበት በከፊልና ሙሉ ለሙሉ ተስተጓጉሏል፤ ግጭቱ በተከሰተባችዉ አካባቢዎች አቅራቢያ አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች እንዲጨናነቁ እና መደበኛ ከሆነዉ አቅማቸዉ በላይ አገልግሎት እንዲሰጡ አስገድዷል” ብሏል ጤና ሚኒስቴር፡፡

በመሆኑም ለህብረተሰቡ ቀጣይነት ያለዉ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል እና አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ይህንን የሃብት ማሰባብሰብ እና ድጋፍ ስራን ለማስተባበር የጤና ሚንስቴር የባለሙያ ቡድን ያቋቋመ መሆኑን ገልጾ በግለሰብም ሆነ በቡድን ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊ መረጃ እና ትብብር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለዚህ አደጋ ምላሽ ለመስጠት እንዲያግዝ ሁሉቀፍ ከግጭት ጋር የተያያዘ ድንገተኛ አደጋ የጤና ምላሽ ስርዓት አቋቁሞ ዘርፈ ብዙ ርብርብ እያደረገ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

(ደመቀ ከበደ - አዲስ አበባ)


2 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now