ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ የ$40 ቢሊየን ሙዋዕለ ፍሰት በማድረግ 71 የንፁህ ኃይል ፕሮጄክቶችን ግብር ላይ ለማዋል ተልማለች።
ይህም በ2037 የ35,000 ሜጋዋት ጂኦተርማል ብቃት እንደሚያስገኝላትና የምሥራቅ አፍሪካ መጠነ ሰፊ ኃይል አቅራቢ አገር እንደሚያደርጋት ግምት አሳድሯል።
በስምጥ ሸለቆ አካባቢ ባሉ ቱሉ ሞዬ፣ አሉቶ ላንጋኖና ኮርበቲ ፕሮጄክቶች ጅማሮ ሂደት ወደ እንቃስቃሴ እየገባ ሲሆን 14 የሶላር ኃይል ፕሮጄክቶች በመጪዎቹ 10 ዓመታት ግብር ላይ እንዲውሉ ተወጥኗል።
በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥም 24 የነፋስ ኃይል ፕሮጄክቶች ሥራ ላይ እንደሚውሉ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 5,000 ሜጋዋት ታዳሽ ኃይል አላት።
Afriki21
የመከላከያ ስምነት
የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን መንግሥት ከዩናትድ ስቴትስና እንግሊዝ ጋር በሽርካ ሊገነባ ላሰበው ባለ ኑክሊየር ሰርጓጅ መርከብ ከመርህ አኳያ ድጋፍ መስጠቱን አስታወቀ።
የፌዴራል መንግሥቱ ቀደም ሲል የአውስትራሊያን ውኃዎችና ፍላጎቶችን ለማስጠበቅ ሲል የ$90 ቢሊየን ስምምነት ከፈረንሳይ የባሕር መከላከያ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
ይሁንና በአሁኑ AUKUS ተብሎ በሚጠራው የሶስትዮሽ ስምምነት ሳቢያ የፈረንሳዩን ስምምነት ሰርዟል።
የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ስምምነቱ የኣገር ውስጥ ሲቪል ኢንዱስትሪ፣ የኑክሊየር መሳሪያዎችን መገንባትን ግድ የማይልና የኑክሊየር መስፋፋትን የመከላከል ቃል ኪዳንን እስካልተፃረረ ድረስ ሰርጓጅ መርከቦቹ ለብሔራዊ ደኅንነት ትሩፋት እንደሚኖራቸው በመናገር የሌበርን አቋም ይፋ አድርገዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን የኑክሊየር ኃይል የታጠቁ የአውስትራሊያ ሰርጓጅ መርከቦች የአገራቸውን ውኃ ማቋረጥ እንደማይችል ከወዲሁ አስታውቀዋል።

