የአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች አገራት ምደባ ይፋ ሆነ

*** አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

News

Dina Mufti, spokesman of the Ethiopian Foreign Ministry. Source: MoFA spokesperson Office

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርነትና የአምባሳደርነት ማዕረግ በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተሿሚዎች የተመደቡባቸው አገራት መገለፁን አስታወቁ። 

ቃል አቀባዩ ይህን ያስታወቁት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 8 ለአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች  በሰጡት መግለጫ ነው። 

አምባሳደር ዲና እንዳሉት

1. አምባሳደር ተፈራ ደርበው ---ጃፓን

2. አምባሳደር ደሴ ዳልኬ---ደቡብ ኮሪያ

3. አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ---አሜሪካ

4. አምባሳደር ባጫ ደበሌ__ኬንያ

5. አምባሳደር ሐሰን ኢብራሂም--ግብፅ

6. አምባሳደር ዳባ ደበሌ --ሩዋንዳ

7. አምባሳደር ጀማል በከር--ፖኪሲታን

8. አምባሳደር ፈይሰል አሊይ__ኳታር

9. አምባሳደር ኢሳያስ ጎታ---ሞሮኮ

10. አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው--አውስትራሊያ

11. አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ---ስዊዲን

12. አምባሳደር ፍቃዱ በየነ--ኤርትራ

በሌላ በኩል ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ሆኖ በተለያዩ ሀገሮች የተሾሙ አምባሳደሮች፦

13. አምባሳደር ጣፋ ቱሉ--ብራዚል

14. አምባሳደር ዶ/ር ገነት ተሾመ--ኩባ

15. አምባሳደር ሽታዬ ምናለ-- ኮትዲቯር

16. እምባሳደር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ-ኢንዶኔዥያ

17. አምባሳደር ረሻድ መሀመድ-- ዝምባብዌ

በቆንስል ጄነራልነት የተመደቡ፤

18. አምባሳደር አንተነህ ታሪኩ -ገዳሪፍ

19. አምባሳደር አክሊሉ ከበደ--ዱባይ

20. አምባሳደር ሰይድ መሐመድ-ሀርጌሳ

21. አምባሳደር አወል ወግሪስ--ባህሬን

በምክትል የሚሲዮን መሪነት፦

22. አምባሳደር አሳየ አለማየሁ--ጋና

23. አምባሳደር ኃይላይ ብርሃነ--ጀርመን

24. አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት--ሕንድ

25. አምባሳደር ዮሴፍ ካሳዬ--ኒው ዮርክ

26. አምባሳደር ዘላለም ብርሃን--ዋሽንግተን

27. አምባሳደር ፍርቱና ዲባኮ-- ቤልጅየም

28. አምባሳደር ወርቃለማሁ ደሰታ --ኬንያ

29. አምባሳደር ውብሸት ደምሴ--እንግሊዝ

30. አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል--ፓኪስታን

መመደባቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደራቱ በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል። 

[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]


2 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now