አማራ ባንክ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛውን የመነሻ ካፒታል በማስመዝገብና ከ70 በላይ ቅርጫፎችን በመክፈት ሥራውን ጀመረ

ከነሐሴ 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የምስረታ ስራዎችን ሲያካሄድ የቆየው አማራ ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ታሪክ ከፍተኛ የሆነው የባለአክሲዮን ቁጥር እና መነሻ ካፒታል በመያዝ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ።

News

Source: AB

የባንኩ የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ መላኩ ፈንታ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለፁት አማራ ባንክ ከቀደሙት ባንኮች ብዙ በመማር በተለይም ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ለማቀፍ ተደራጅቶ “ከባንክ ባሻገር” በሚል መሪ ቃል ተመስርቷል።

የባለአክሲዮኖች 50 በመቶ ድርሻ ከአዲስ አበባ፣ 30 በመቶ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች እና 20 በመቶው ከአማራ ክልል መሆኑ ተገልጿል።

News
Source: AB

ባንኩ ቅዳሜ ሰኔ 11 በይፋ ስራ መጀመሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በአንበሳ የህዝብ ትራንስፖርት ነፃ እንዲሆን እና በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት ለሚወልዱ አራሶች ስጦታ እንዲሁም ለተወለዱት ህፃናት 2 ሺህ ብር ገቢ የተደረገበት የባንኩ ሂሳብ እንደሚያስረክብ የቦርድ ሊቀ መንበሩ ገልፀዋል።

ለገሃር በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

News
Dr Yilkal Kefale (L), Agegnehu Teshager (C), and Dr Yinager Dessie (R). Source: AB

ባንኩ ከ6.5 ቢልየን ብር በላይ የተፈረመ ካፒታል ይዞ ስራዉን የጀመረ ሲሆን ከዛሬ ሰኔ 11 ጀምሮ በ72 ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ባንኩ በሰኔ ወር መጨረሻም የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ100 በላይ ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል።

[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]


1 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now