የሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ

*** በሕዳሴ ግድብ የኃይል ምንጭ ጅማሮ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሃን መባቻ ነው" ብለዋል።

Homeland Report

This general view shows the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) in Guba, Ethiopia, on February 19, 2022. Source: Getty

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ዛሬ እሑድ የካቲት 13 2014 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።

የሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ሥራ በይፋ መጀመርን ያስታውቁት በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በስፍራው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው።

ዛሬ ሥራ ላይ በዋለው አንድ ተርባይን አማካይነት መመንጨት የጀመረው ኃይል 375 ሜጋ ዋት ሲሆን የሕዳሴ ግድብ 13 ተርባይኖችን የያዘ ነው።

ግድቡ በሁለተኛ ዙር ሙሌቱ 13 ቢሊየን ኪዩቢክ ውኃ ያቋረ ሲሆን፤ የግንባታ ወጪው በተለያዩ አስባቦች ከታሰበለት 80 ቢሊየን ብር አልፎ 163 ቢሊየን ብር ደርሷል።  

በሥነ ሥር ዓቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኃይል ምንጭ ጅማሮውን አስመልክተው "ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሃን መባቻ ነው" ብለዋል።

የግድቡ ሓይል ምንጭ ጅማሮ ለአካባቢው አገራትም ጭ ምር "ብሥራት" መሆኑን ተናግረዋል።  

ለፕሮጄክቱ እውንነት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጀመሮ በተከታታይ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ያበረከቱ ቀደምት የኢትዮጵያ መሪዎችንም በስም ጠቅሰው አመስግነዋል። 

ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኃይል በመሸጥ 580 ሚሊየን ዶላርስ ያህል ዓመታዊ ገቢ ልታገኝበትም እንደምትችል ተነግሯል።  

 

 


1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now