የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ቃለ መሐላ ፈፀሙ

*** ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆኑ

News

Source: M.Ashenafi

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ዕለተ ሰኞ የካቲት 14 - 2014 ባካሔደው ልዩ ስብሰባ የ11 አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት ማፅደቁን ይፋ አደረገ፡፡

 

ምክር ቤቱ ቀደም ሲል ጥር 27 -  2014 የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ሕብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው የ42 ዕጩ ኮሚሽነሮችን ስም ዝርዝር፣ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምዶችን አካትቶ አቅርቦ ነበር።

 

በዛሬው ዕለት  ምክር ቤቱ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢን አካትቶ ለ11 አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ይሁንታውን ቸሯል። 

 

ኮሚሽነሮቹም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት መዓዛ አሸናፊ አማካይነት ቃለ መሐላ ፈፅመዋል። 

 

 

1. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ – ሰብሳቢ

 

2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ – ምክትል ሰብሳቢ

 

3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ

 

4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ

 

5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን

 

6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

 

7. አቶ ዘገየ አስፋው

 

8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም

 

9. አምባሳደር መሐሙድ ድሪር

 

10. አቶ ሙሉጌታ አጎ እና

 

11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ ናቸው።


1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now