‘አድዋስ’ ሙዚቃዊ ቲያትር የካቲት 22 የአድዋ በዓል ዋዜማ ላይ በወዳጅነት አደባባይ ለዕይታ ሊበቃ ነው

*** “ 'አድዋስ' በጽሁፍ እና በዝግጅት የላቀ ጥበብ የታየበት ነው፤ ቲያትሩ በአጭር ጊዜ ተሰርቶ ሊያልቅ የቻለው እውነተኛ የአድዋ ልብ ባላቸው ሰዎች የተዋቀረ ቡድን መሰራቱ ነው" አዘጋጅ ተስፋዬ እሸቱ

Homeland Report

Source: Adwas

350 ሰዎችን ያሳተፈው ‘አድዋስ’ ሙዚቃዊ ትያትር የካቲት 22 የአድዋ በአል ዋዜማ በወዳጅነት አደባባይ ለእይታ ሊበቃ ነው።

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተዘጋጅቶ ያለቀው ይህ ሙዚቃዊ ትያትር እንደ አበበ ባልቻ፣ ተፈሪ ዓለሙ፣ ትግስት ግርማ እና አስመላሽ ታምራትን ጨምሮ ከህጻን እስከ አንጋፋ ተዋንያን እና 150 የዳንስ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

በያሬድ ሹመቴ ተደርሶ በተስፋዬ እሸቱ ፕሮዲውስ የተደረገው ይህ ትያትር ባለቤትነቱ የጉዞ አድዋ ሲሆን ትላንት የካቲት 15/ 2014 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

የቲያትሩ ደራሲ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ስለ ትያትሩ ሲገልጽ፣ “አድዋ የብዙ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ታሪክ ሲሆን ሃሳቡን ወደ ትያትር ለመቀየር ብዙ ጊዜ ፈጅቶብናል፤ ወደስራ የገባነው ጥር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ላይ ነው” ብሏል።

ደራሲው ቲያትሩ ሰርቶ ለማጠናቀቅ የ1 ወር ጊዜን ብቻ እንደወሰደም ተገልጿል። ለትያትሩ ዝግጅትም የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር የ25,000 ብር እርዳታ እንዳደረገ ማወቅ ተችሏል።

የቲያትሩ ፕሮዲውሰር የሆነው ተስፋዬ እሸቱ፣ “በፊልም ጽሁፍ እና በዝግጅት የላቀ ጥበብ የታየበት ነው፤ ቲያትሩ በአጭር ጊዜ ተሰርቶ ሊያልቅ የቻለው እውነተኛ የአድዋ ልብ ባላቸው ሰዎች የተዋቀረ ቡድን መሰራቱ ነው፤ የ 350 ሰው ባህሪን ተረድቶ የተዋጣለት ስራ መሰራት መቻሉ እውነትም የትያትር ዝግጅቱ አባላት የአድዋ ልብ ያላቸው ስለመሆኑ ያሳያል” ብሏል።


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now