SKIP TO MAIN CONTENT

ፕሮፌሰር ካሣሁን ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

*** ፕ/ር ካሣሁን ላለፉት 36 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና ተመራማሪነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ከፍተኛ የኃላፊነት እርከኖች አገልግለዋል።

News
Prof Kassahun Berhanu. Source: K.Berhanu

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (PSIR) ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፈሰር ካሣሁን ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

 ፕ/ር ካሣሁን በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 15/2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አሳውቋል።

ፕ/ር ካሣሁን ላለፉት 36 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና ተመራማሪነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ዕርከኖች አገልግለዋል።

በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማበርከትም ይታወቁ ነበር፡፡

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ነገ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በየካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ይፈፀማል፡፡


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now