የፀሐይ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ መስፈን ባንኩ 30 ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በመግለጽ በቅርቡ የቅንጫፎቹን ብዛት ወደ 50 ያሳድጋል ብለዋል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታዬ ዲበኩሉ ባንኩ በ373 ባለአክሲዮኖች: በ734 ሚሊዮን ብር የተከፈለና በ2.9 ቢሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታል ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን አስታዉቀዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዢዉ ዶ/ር ይናገር ደሴ ከለዉጡ ወዲህ በርካታ ባንኮች እየተቋቋሙ መሆናቸዉን በመግለጽ በሃገሪቱ ያሉት ባንኩች ቁጥር 30 የማይክሮ ፋይናንሶች ብዛት ደግሞ 40 መድረሱን ተናግረዋል።
ባንኮቹ የገጠሩንና የከተማዉን ማህበረሰብ ኑሮ ከማሻሻል ረገድ ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል ብለዋል።
ፀሐይ ባንክ በቴክኖሎጂ ዘመን የተቋቋመ ባንክ እንደመሆኑ መጠን የተሻለ የባንክ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
ፀሐይ ባንክን ጨምሮ በሃገሪቱ ዉስጥ ያሉ ባንኮችን አቅም ለማሳደግ ብሄራዊ ባንክ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ባንኩ ምረቃዉን ምክንያት በማድረግና ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ለጌርጌሴኖን የመረዳጃ ማህበር 300 ሺህ ብር : ኒያ ፋዉንዴሽን ጆ ኦቲዝም 300 መቶ ሺህ ብር: ለኩላሊት የበጎ አድራጎት ድርጅት 500 ሺህ ብር: ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የ500 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።