SKIP TO MAIN CONTENT

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ

*** የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባእኤና ምክትል አፈ ጉባኤዎችም ተመርጠዋል።

Shimelis Abdisa, President of Oromia State.
Shimelis Abdisa, President of Oromia State. Source: S.Abdisa

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ተከትሎ ለአምስት ዓመት የሚዘልቅ የጨፌ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስከረም 15, 2014 ተመሥርቷል።

አዲሱ ጨፌ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው የመንግሥት ምሥረታ ጉባኤው የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዚደንት ዳግም መርጧል።

የካቢኔ አባላትንም ስይሟል።   

ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤው ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማንን አፈ ጉባኤ፤ አቶ ኤልያስ ኡመታን ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል። 

ተመራጭ አፈ ጉባኤዎቹም ቃለ መሐላ ፈጽመው የሥራ ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል። 

የክልልና የፌዴራል መንግሥታት ምሥረታው የጊዜ ሠንጠረዥ ተይዞለታል።

በዚህም መሠረት፤

  • መስከረም 20, 2014 የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ
  • መስከረም 20, 2014 የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ
  • መስከረም 20, 2014 የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ
  • መስከረም 20, 2014 የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ
  • መስከረም 20, 2014 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስረታ
  • መስከረም 21, 2014 የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምስረታ
  • መስከረም 22, 2014 የደቡብ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ
  • መስከረም 24, 2014 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ምስረታ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል። 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now