የኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነት ሊመለስ ይችላል ተባለ

ከተያዘው የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ አንስቶ የተሰረዘው የኢትዮጵያ የአፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) እድል ተጠቃሚነት በመጪው ዓመት ዳግም ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰንዶካን ደበበ ገለጡ፡፡

News

A general view of a garment factory at the Hawassa Industrial Park in Hawassa, southern Ethiopia. Source: Getty

ከተያዘው የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ አንስቶ የተሰረዘው የኢትዮጵያ የአፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) እድል ተጠቃሚነት በመጪው ዓመት ዳግም ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰንዶካን ደበበ ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ አሜሪካ የአፍሪካ አገራት የተለያዩ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ ወደ ግዛቷ እንዲያስገቡ ከሚፈቅደው የአጎዋ ሥርዓት መመለስ ዜና የመጣው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዩ ይልማ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ተከትሎ ነው፡፡

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን በዚህ ውይይት ወቅት የኢትዮጵያ የአጎዋ እድል ጠቃኒነት እንደሚመለስ አረጋግጠዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በተያዘው ዓመት ታህሳስ ወር ኢትዮጵያ ከአጎዋ ተጠቃሚነት እድል እንድትሰረዝ የቀረበውን ስምምነት የፈረሙት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ ከተላለፈባት ከዚህ ውሳኔ በኋላ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ገበያ ለቀው እንደሚወጡ ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

በዚሁ ሰበብ ከሰሞኑ 3 ሺሕ ሠራተኞች ከሥራቸው ሊፈናቀሉ መሆኑ ተሰምቷል፡፡


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now