የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደሮች ጥር 18 2014 ሹመት ሰጡ፡፡
ከ27 የአምባሳደርነት ሹመት ውስጥ 16ቱ የባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት፣ 11ዱ የአምባሳደርነት ሹመቶች መሆናቸውን የፕሬዚደንቷ ጽሕፈት ቤት ገልጧል።
በሹመት አሰጣጡ መሠረት፤
- አቶ ተፈራ ደርበው፣
- አቶ ደሴ ዳልኬ ፣
- ዶክተር ስለሺ በቀለ ፣
- ጀነራል ባጫ ደበሌ ፣
- ጀነራል ሀሰን ኢብራሒም ፣
- ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ፣
- ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ ፣
- አቶ ረሻድ መሀመድ ፣
- አምባሳደር ጀማል በከር ፣
- አቶ ፈይሰል አሊይ ፣
- አቶ ኢሳያስ ጎታ ፣
- አቶ ጸገአብ ክበበው ፣
- አቶ ጣፋ ቱሉ ፣
- ዶክተር ገነት ተሾመ ፣
- አቶ ዳባ ደበሌ እና
- አቶ ፈቃዱ በየነ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነዋል፡፡
በአምባሳደርነት ማዕረግም፤
- አቶ አሳዬ አለማየሁ፣
- አቶ ሃይላይ ብርሃነ፣
- አቶ አወል ወግሪስ፣
- ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት፣
- አቶ አንተነህ ታሪኩ፣
- አቶ አክሊሉ ከበደ፣
- አቶ ሰይድ መሐመድ፣
- አቶ ዮሴፍ ካሳዬ፣
- አቶ ዘላለም ብርሃን፣
- ወይዘሮ ፍርቱና ዲባኮ እና
- አቶ ወርቃለማሁ ደስታ ተሾመዋል።
አገራዊ የምክክር ኮሚሽን
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክት ቤት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከቀረቡት 632 ዕጩዎች መካከል 42ቱን መዝኖ መለየቱን በምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አማካይነት አስታወቀ፡፡
አፈ-ጉባኤው ምንም እንኳ 42 ዕጩዎች በማጣሪያ ሂደቱ ወቅት ቢለዩም፤ ከመላ አገሪቱ በዕጩነት የቀረቡትን 632 እጩ ኮሚሽነሮች ለመለየቱ ሂደት በርካቶች ለኮሚሽነርነት የሚያበቃ የሥራ ልምድና ዕውቀት ያላቸው መሆኑን ገልጠዋል።
ቀጣዩ ሂደት የሚሆነውም፤ በ42ቱ ዕጩዎች የትምህርት ብቃት ደረጃና የካበተ የሥራ ልምድን አስመልክቶ ከሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራር አካላት ጋር በሚካሔድ ምክክር ግብአት ማሰባሰብ ይሆናል።
በታካይነትም የእጩዎቹ ማንነት በምክር ቤቱ ድረ-ገጽና ማኅበራዊ ሚዲያ ይፋ በማድረግ ተጨማሪ ግብአቶች ይሰበሰባሉ።
ኮሚሽኑ የሚኖሩት 11 ኮሚሽነሮች ሲሆን፤ የኮሚሽኑን ሥራ በኃላፊነት የሚመሩ አንድ ዋና ኮሚሽነርና አንድ ምክትል ኮሚሽነር ይኖሩታል።
በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 13 መሠረትም 11ዱ ዕጩ ኮሚሽነሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት መመዘኛዎቹን አሟልተው መገኘታቸው ተመርምሮ ሹመታቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅድቅ እንዲቸርው ይደረጋል።
በአሁኑ ወቅት ከአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ስየማ፣ የምክክሩ ሂደትና ከጋራ ብሔራዊ ስምምነት ላይ የመድረስ ስኬት ጉዳይ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን የስጋትና የተስፋ ቀልቦች ስቦ ያለ ጉዳይ ነው።

