በወሎና አፋር ግንባሮች ወታደራዊ ማጥቃቶች ቀጥለዋል

*** የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሰላምና ዕድገት ማዕከልን ፈቃድ ሰረዘ

Homeland Report

Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed. Source: FBC

የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አዝማችነት በወሎና አፋር ግንባሮች ማጥቃቶቹን አጠናክሮ መቀጠሉንና የተወሰኑ ሥፍራዎችን ተቆጣጥሮ ወደፊት እያመራ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።  

በኮሙኒኬሽን አግልግሎት መግለጫ መሠረትም፤ የመከላከያ ሠራዊት በባቲ ካሳጊታ ግንባር በተካሔደ አስለቀቆ በቡርቃና በባቲ ዙሪያ ገባ የሚገኙ ተራሮችን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ወደ ባቲና ኮምቦልቻ እያመራ መሆኑን ገልጧል።

በአፋር ግንባርም ጪፍቱን ጨምሮ ጭፍራና አካባቢዋን ከሕወሓት ታጣቂዎች እጅ ማውጣቱን አክሎ ይፋ አድርጓል። ቀጣዩ ማጥቃትም ወደ ባቲና ኮምቦልቻ መሆኑን አመልክቷል።

በሌላ በኩል በተቀናቃኝ ተፋላሚው ሕወሓት ቃል አቀባይ በኩል ዓርብ ዕለት መቀሌ ከተማ ላይ የአየር ጥቃት እንደደረስ የተገለጠ ሲሆን፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየወሰዳቸው ባሉ የማጥቃት እርምጃዎች ላይ መግለጫዎችን አላስደመጡም።

የሰላምና ዕድገት ማዕከል

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሰላምና ዕድገት ማዕከል ቅርንጫፍ የሆነውን ሰላምና ዕድገት ማዕከልን ፈቃድ ሰረዘ። 

የባለስልጣኑ መሥሪያ መሥሪያ ቤት የማዕከሉን ፈቃድ ለመሰረዝ የበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ "የአገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ፈቃድ ለመሰረዝ ሊያዝ ይችላል ተብሎ በተደነገገው መሠረት የሰላምና ልማት ማዕከል የሲቪል ማሕበረሰብ የምዝገባ ድርጅት የምዝገባ ምስከር ወረቀት (ፈቃድ) ከዛሬ ሕዳር 17 / 2014 የተሰረዘ መሆኑን አስታውቃለሁ" ብሏል።

ባለስልጣኑ አክሎም "የመሥሪያ ቤታችን የሲ/ማ/ድ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬትም አግባብነት ካለው አካል ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የድርጅቱን ንብረት እንዲረከብ አሳስባለሁ" ሲል የማዕከሉ ንብረት በቁጥጥር ስር እንዲውል መመሪያ መስጠቱን አስታውቋል።    

ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሪያ ዕዝ ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የበቃው ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ዕድገት ማዕከል የውጭ አገር አምባሳደራትንና በባሕር ማዶ የሕወሓት ተጠሪን ጋብዞ ካካሄደው ስብሰባ ጋር ተያያዥነት ያለው መሆንና አለመሆኑን አስመልክቶ በግልፅ አልሰፈረም።   


2 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now