ዛሬ ማለዳ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2014 የበጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፍሬሕይወት ታምሩ በበጀት ዓመቱ 70 ቢልዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የእቅዱን 87 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገለፃ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶችም ከ146 ሚልዮን ዶላር በላይ ተገኝቷል
ኢትዮ-ቴሌኮም የአገልግሎት ተጠቃሚን ቁጥር ለማሳደግ ከታቀደው እቅድ 104 በመቶ ማሳካቱን ዋና ስራ አስፈፃሚ ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ እንዳሉት የአገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ብዛት 66 ነጥብ 59 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸው የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ከባለፍው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ18 ነጥብ 4 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት ጨምሮ ሌሎች በሀገሪቱ የተስተዋሉ አለመረጋጋቶች ለቴሌኮም መሰረተ ልማት መውደም እና ለእቅዱ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]