ኢትዮጵያም በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ከተመዘገቡት የምትመደብ ብቻ ሳይሆን በእስካሁኑ የሻምፒዮናው ተሳትፎ ታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ ያገኘችበትና በጀግኖች አትሌት ልጆቿ ደምቃ የታየችበት ነው።
ይህንንም አስመልክቶ ለጀግኖች አትሌቶች ከትናንት ምሽት የጀመረ የጀግና አቀባበል እየተደካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሻምፒዮናው 4 ወርቅ፣4 ብር እና 2 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በማምጣት ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም 2ኛ በመውጣት ማጠናቀቁ ይታወቃል፡፡

Welcoming ceremony. Source: P Record
[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]