የኢፌዴሪ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ተክስቶ ላለው የሰላም መደፍረስ ሰላማዊ መፍትሔ ለማስገኘት እንዲያስችል አንድ ተደራዳሪ ቡድን ሰይሟል።
ሰባት አባላት ያሉት የተደራዳሪ ቡድኑ በገዢው ብልፅግና ፓርቲ ስራ አሥፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ አማካይነት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በሚያስጠብቅና ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስከብር ማዕቀፍ ውስጥ እንዲደራደር የውክልና ኃላፊነት የተሰጠው መሆኑ ተገልጧል።
የሰላም ተደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢና አባላት ዝርዝርም በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አማካይነት ሰኞ ሰኔ 20 / 2014 ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሠረት፤
- አቶ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢ
- ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አባል
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ አባል
- አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር አባል
- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አባል
- ሌተና ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ አባል
- ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር አባል ሆነው ተመድበዋል።
Share

