"ሕወሓት ለሰብዓዊ እርዳታዎች ተደራሽነት ሲባል የታወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ወደ ጎን ገፍቶ አጋጣሚውን ለትንኮሳ አውሎታል" ቢልለኔ ስዩም

*** የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ

Press Secretary for the Office of the Prime Minister of Ethiopia, Billene Seyoum.

Press Secretary for the Office of the Prime Minister of Ethiopia, Billene Seyoum. Source: Getty

ለሰብዓዊ ድጋፍና ለአርሶ አደሮች እርሻ ሥራ የተተገበረው የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ በሕወኃት ጠብ ፈጣሪነት ባለመተግበሩ የትግራይ ሕዝብ ለተጨማሪ ችግር እየተዳረገ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎች ኃላፊ ቢለኔ ሥዩም ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ የትግራይ አርሶ አደሮች የዝናቡን ወቅት እንዲጠቀሙ ለማስቻልና ለሰብዓዊ እርዳታዎች ተደራሽነት ሲባል የታወጀውን የተናጥል የተኩስ አቁም ወደ ጎን ገፍቶ  አጋጣሚውን ለትንኮሳ አውሎታል ብለዋል።

እንደ ቢለኔ ገለፃ ሕወኃት ከትግራይ አልፎ የአማራ አርሶ አደሮችንና የአፋር አርብቶ አደሮችን እንዲፈናቀሉና እንዳይረጋጉ እያደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሕፃናትንና ሲቪልያንን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ ሽፋን በማድረግ በአፋርና በአማራ ክልሎች በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ ጥቃት እየሰነዘረ ነው ያሉት ቢለኔ "በአሸባሪ ቡድኑ ምክንያት በተለይም በሁለቱ ክልሎች ያሉ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የዕለት ተዕለት ህይወታቸው ታውኳል" ብለዋል። "ህጻናትን አደንዛዥ እጽ በማስጠቀም ወደ ጦርነት እያሰማራ ነው። ይህንን ድርጊትም ለዓለም አቀፍ ተቋማት አሳውቀናል" ሲሉም አክለዋል። 

የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነቱ በምን ሁኔታ ላይ እንደሆነ የተጠየቁት ብለኔ " የእርዳታ ማመላለሻ ኮሪደሮች በአሸባሪው ሕወኃት ተዘግተዋል፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ደጋፊ ናቸው ያላቸውን የትግራይ ተወላጆችንም መርጦ እየገደለ ነው፤ የተጠናጠል የተኩስ አቁሙ ተወስኖ መከላከያ ከመቀሌ ሲለቅ ለሰብዓዊ ድጋፍ ተብሎ በእህል ማከማቻ መጋዘን የተቀመጠ ከ 400 ሺ ኩንታል በላይ የምግብ ክምችት ለራሱ እያዋለው ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

የውጭ ቋንቋ ኃላፊዋ ቢለኔ ሕወኃት የኤርትራ ስደተኞች በሚገኙበት ጣቢያ ጥቃት ፈፅሞ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ንብረቶችን መዝረፉን የገለፁ ሲሆን እስከሁን ስድስት ኤርትራዊ ስደተኞች መገደላቸው ተረጋግጧል ብለዋል። 

በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ ክልሎች ለአገር ህልውና በአንድነትና በትብብር ቆመዋል ያሉት ብለኔ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችና በዲያስፖራው ዘንድም ሕወኃትን የሚያወግዙ ሰልፎች መከናወናቸውን አንስዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የሕወኃት ወንጀልና ጠብ አጫሪነት እያየለ ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና የውጭ ሚዲያዎች በዝምታ ማለፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀው ይህ ሁኔታ ለአንድ ወገን ያደላ አተያይ መኖሩን የሚያሳይ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


2 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now